Wir verwenden Cookies, um die Benutzerfreundlichkeit dieser Webseite zu erhöhen (mehr Informationen).

Prof. Dr. Werner Gitt

እንዴት መንግሥተ ሰማያት መግባት እችላለሁ?

Die grundlegende Frage, die suchende Menschen sich stellen, wird hier von Prof. Dr. Werner Gitt beantwortet. "Wie findet man den Himmel?" Auf jeden Fall nicht durch eigene Anstrengungen oder Konzepte. "Was aber bringt uns wirklich in den Himmel?" Gott hat die Einladungen für den Himmel schon verteilt wie im Gleichnis des Menschen, der zu einem großen Fest Einladungen verschickte. Doch viele Menschen redeten sich heraus.

Prof. Dr. Gitt ruft dazu auf, nicht so "kurzsichtig" wie diese Leute zu sein. Jesus will uns vor der Hölle erretten und diese wird kein Vergleich zu der sogenannten "Hölle von Auschwitz" sein. Er hat am Kreuz für unsere Schuld bezahlt, wir müssen diese Einladung nur annehmen, dann ist ein Platz im Himmel "gebucht". Ein Entscheidungsgebet soll den Lesern dabei helfen.

Dieses Traktat eignet sich besonders gut zur Weitergabe an suchende Menschen!

8 Seiten, Best.-Nr. 120-72, Kosten- und Verteilhinweise | Eindruck einer Kontaktadresse


እንዴት መንግሥተ ሰማያት መግባት እችላለሁ?

ብዙ ሰዎች ስለ ዘላለማዊ ነገር ማሰብን አይፈልጉም፡፡ ስለሞት እንኳን የሚያስቡ ሰዎች ከዚያ በኋላ ስለሚሆነው ማሰብን አይፈልጉም፡፡ በE.T በተባለው ፊልም ላይ እንደ ልጅ በመሆን ዋና ገጸ ባህርይውን የተጫወተችው አክትረስ ድሬው በኤርሞሪ በ1975 እ.ኤ.አ ተወልዳ በ28 ዓመቷ ላይ ‹ከድመቴ በፊት ከሞትኩ ከዚያም በኋላ በእርሷ የቀረው ሰውነቴ ተበልቶ ቢያንስ በውስጧ መኖርን እፈልጋለሁ‹‹ ብላለች፡፡ ይህ አለማስተዋልና ወደፊት ያለውን ያለማየት ፍርሃት አይደለምን?

ኢየሱስ በምድር በነበረበት ወቅት ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፡፡ የእነርሱም ጥያቄ በአሁን እና በቅርብ ጊዜ ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር፡

  •  10 ለምፃሞች ለመፈወስ መፈለጋቸው (ሉቃ 17፡13)
  •  ዕውሮች ማየት መፈለጋቸው (ማቴ 9፡27)
  •  አንድ ሰውም ኢየሱስ በውርስ ጉዳይ ላይ እንዲረዳው በመፈለግ (ሉቃ 12፡13-14)
  •  ፈሪሳዊያን ኢየሱስን ለማጥመድ በመፈለግ ለቄሳር ግብር ስለመስጠት (ማቴ 22፡17)

ደግሞ ጥቂት ሰዎች ወደ ኢየሱስ ይመጡና ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት እንዴት እንደሚችሉ ያደምጡት ነበር፡፡ ባለጠጋና ህግ አዋቂ የሆነ ወጣት ወደ ኢየሱስ በመቅረብ ‹‹ቸር መምህር የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? አለው›› (ሉቃ 18፡18) ነገር ግን ያለውን ሁሉ እንዲሸጥና ኢየሱስን እንዲከተል ተነገረው ሆኖም ባለጠጋ ስለነበረ የኢየሱስን ምክር ሳይቀበል ቀረ ከመንግሥተ ሰማያትም መንገድ ወጣ፡፡

በሌላ በኩል ድግሞ፤ መንግሥተ ሰማያትን ፈልገው ሳይሆን ከኢየሱስ ጋር በነበራቸው ጥያቄ አማካኝነት ድንገት በሰሙት የመንግሥተ ሰማይን መንገድ ትምህርት በማስተዋል ይህን ዕድል በቀጥታ ተጠቅመውበታል፡፡ ዘኬዎስ ለብዙ ጊዜ ኢየሱስን ማየት ይፈልግ ነበር ባገኘውም ጊዜ ከጠበቀው በላይ ነበር የሆነለት በአንድ ማዕድ ላይ ሆነው ኢየሱስ “ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል“ (ሉቃ 19፡9) መንግሥተ ሰማይን አግኝቷል በማለት ተናግሯል፡፡

እንዴት መንግሥተ ሰማይን መውረስ እችላለሁ?

ከዚህ ቀደም እንደተመለከትነው ማየት የምንችለው ነገር

  •  የእግዚአብሔርን መንግሥት የምናገኛት በተወሰነ ጊዜ ብቻ መሆኑ ነው፡፡ ውድ አንባቢዎች ይህ ማለት የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት መወሰን አሁን መሆኑን እንድታውቁ ማለት ነው፡፡
  •  ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመልካም ስራዎች አማካኝነት መግባት አይቻልም፡፡
  •  ያለ ምንም ቅደመ ዝግጅት የእግዚአብሔርን መንግሥት መውረስ ይቻላል፡፡

የእኛ ወደ እግዚአብሔር መንግስት የመግቢያ አሰተሳሰቦች ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ሃሳብ ካልሆኑ ስህተት ናቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ዘፋኝ ስለ ታዋቂ እና አስቂኝ ስለሆነ የሰርከስ ሰራተኛ ስለነበረው በመጨረሻ ጡረታ ስለወጣው ሰው ሲዘፍንለት ‹‹ይህ ሰው ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባል ምክንያቱም ብዙዎችን አስቋልና›› (ብሎ ዘፍኗል)፡፡ አንዲት ባለጠጋ የሆነች ሴት ለ20 የሚደርሱ ድሆች ቤት ሰርታ በመስጠትና ከክፍያ ነፃ በማድረግ እንዲኖሩ ካደረገች በኋላ ለእርሷ ግን በቀን ለአንድ ሰዓት ያህል ስለ ዘላለም ሕይወት እንዲጸልዩላት ታደርግ ነበር፡፡

ነገር ግን በእውነት እንዴት ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት እንችላለን?

ኢየሱስ በምሳሌ በማስረዳት አስተማረ፡፡ ይህም ምሳሌ እግዚአብሔርን የሚያሳይ ሲሆን ይህም አንድ ንጉሥ ታላቅ ግብዣን እንዳደረገ የሚናገር ነበር፡፡ በሉቃስ 14፡16‑24 ንጉሡም ወደ ግብዣው እንዲመጡ መልዕከተኞችን ላከ ነገር ግን ታዳሚዎቹ ምላሻቸው አሳዛኝ ነበር፡፡ ‹‹ሁላቸውም በአንድነት ያመካኙ ጀመር የፊተኛው መሬት ገዝቼ… ሌላው አምስት ጥማድ በሬ ገዝቼአለሁ… ሌላውም ሚስት አግብቼአለሁ ስለዚህ መምጣት አንችልም አሏቸው ኢየሱስም ምሳሌውን በንጉሡ ንግግር ሲጨርስ ‹‹እላችኋለሁ ከታደሙት ሰዎች አንድስ እንኳን እራቴን አይቀምስም ብሎ ተናገረ››

ይህ ምሳሌ እጅግ ግልፅ ነው ምክንያቱም መንግሥተ ሰማይን ማግኘትም ማጣትም እንደሚቻል ይናገራልና፡፡ ዋናው ነገር ጥሪውን መቀበልህና አለመቀበልህ ይሆናል፡፡
ይህ በቀላሉ የሚቻል አይደለምን? በመጨረሻው ዘመን ሰዎች መንግሥተ ሰማይ ቢዘጋባቸው ይህ የሆነው መንገዱን ስላላወቁት ሳይሆን ነገር ግን ስላልተቀበሉት ብቻ ነው፡፡

ምሳሌው ላይ ያየናቸው ሶስቱም ሰዎች ለእኛ መልካም ምሳሌ ሊሆኑን አይችሉም፡፡ ከእነርሱ አንዱም የግብዣውን ጥሪ አልተቀበለምና፡፡ ታዲያ ንጉሡ ወደ ግብዣው ህዝቡን ሁሉ ሲጠራ በወርቅ ፊደላት በተጻፈ ጥሪ አልነበረም ነገር ግን ቀላል በሆነ መንገድ ‹‹ኑ›› በማለት ብቻ ነበረ የጠራቸው እና ይህን ጥሪ በቀላሉ የተቀበለ በታላቁ ግብዣ ላይ ስፍራ ይኖረዋል፡፡ ከዚያም በኋላ ብዙ ሰዎች ወደዚያ ስፍራ መምጣት ጀመሩ፡፡ ንጉሡም ቦታዎችን በማየት ለባሪያዎቹ ‹‹ሂዱና ወደ መንገድና ወደ ከተማ ቅጥር ውጡና ጥሯቸው ቤቴም እንዲሞላ›› አላቸው፡፡

የዚህም ምሳሌ ሃሳብ ለእኛ ምን እንደሚል እንድናይ እፈልጋለሁ፡፡ ይህም በመንግሥተ ሰማያት ስፍራ አለ፡፡
እግዚአብሔር ይህን ስፍራ መጥተህ ውረስ ይልሃል፡፡ እውነተኛ ውሳኔን በመወሰን የዘላለም ቦታ ይኑርህ፡፡ ይህንንም አሁን አድርገው፡፡

ኢየሱስ ከግብዣው ጋር ያዛመደው መንግሥተ ሰማያት ግሩም ስፍራ ስለሆነ ነው፡፡

‹‹ዓይን ያላየው ጆሮም ያልሰማው የሰውም ልብ ያላስተዋለው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው›› 1ቆሮንቶስ 2፡9

በምድር ላይ በየትኛውም ስፍራ በፍጹም መንግሥተ ሰማይን የሚመስላት ነገር የለም፡፡ ልናጣው የማይገባ እጅግ ድንቅ ስፍራ መንግሥተ ሰማያት ነው፡፡ ውድና አስገራሚ ስፍራ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ይህን መንገድ በቀላሉ ከፈተልን፡፡ ወደ እግዚአብሔር መንግሥተ እንድንገባ አደረገን፡፡

ልናደርገው የሚገባ ነገር ቢኖር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መሄድን መፈለግ ብቻ ነው፡፡ ደግሞ የነገን ማየት የማይችሉ ልክ በምሳሌው ላይ እንደተጠቀሱት ሰዎች የእግዚአብሔርን ግብዣ ይንቃሉ፡፡

ደህንነት በጌታ በኢየሱስ በኩል

በሐዋ 2፡21 በጣም አስፈላጊ የሆነ ጥቅስ እናነባለን፡፡ ‹‹የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል›› ይህ ሃሳብ መሰረታዊ የአዲስ ኪዳን ትምህርት ነው፡፡ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ እስር ቤት በሆነ ጊዜ ለእስረኞች አለቃ (ጠባቂ) ንግግሩን ‹‹በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተ እና ቤተሰዎችህም ትድናላችሁ›› ብሎ ጠቅላላ ሀሳቡን ተናግሮታል፡፡ ሐዋ 16፡31 መልዕክቱ እጅግ ግልፅና አጭር ቢሆንም ፍፁም ህይወት ቀያሪም ነበር፡፡

ኢየሱስ ከምን ያድንሃል? በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡ እርሱ ወደ ዘላለም ጥፋት ከሚወስድህ ከገሃነም መንገድ (ጎዳና) ያድናል መፅሐፍ ቅዱስ ሰዎች በመንግሥተ ሰማያት ወይም በገሃነም ለዘላለም እንደሚኖሩ ይናገራል ከሁለቱ የመጀመሪያው መልካም ሲሆን ቀጣዩ ግን ስቃይ ነው በፍጹም ሌላ አማራጭ አይኖርም፡፡ ሰዎች ከሞቱ ከአምስት ደቂቃ በኋላ እንኳ ሞት የመጨረሻው እንዳልሆነ የሚያምኑበትን ዕድል እንኳ አይኖራቸውም፡፡ ሕይወትህ የሚፈረድበት ከኢየሱስ ጋር ባለው ኅብረት ነው፡፡ ያ ደግሞ ዘላለምህን የት እንደምታሳልፍ ይወስናል ማለት ነው፡፡

በፖላንድ ጉብኝት በነበርኩበት ስፍራ ከዚህ ቀደም አውሽዊትዝ ኮንሴንትሬሽን ካምፕ የተባለውን ቦታ ስመለከት በዚህም ቦታ (እ.ኤ.አ1942-1944 በ3ኛው ጀርመን አገዛዝ ስር በሁለተኛው ዓለም ጦርነት) ከ1.6 ሚሊዮን አይሁድ ህዝብ በላይ እጅግ አሰቃቂ ግድያ የተፈጸመ ሲሆን ሰውነታቸውም እንዲቃጠል ተደርጓል፡፡ ይህን በተመለከተ ብዙ ስነፅሑፎች ገሃነም አውሽዊትዝ ነው በማለት ይገልፁታል፡፡ ታዲያ ይህ አባባል 600 ሰዎችን በአንድ ጊዜ ሊያጠፋ የተዘጋጀውን የጋዝ ቻምበር ስመለከት ወደ ሃሳቤ መጣ፡፡ ስቃዩ እንዴት እንደ ነበር ለመገመት እንችላለን ብዬ አላስብም ነገር ግን በእርግጥ ይህ ገሃነም ነበርን? በ1945 እ.ኤ.አ ጀምሮ በዚያ ቻምበር የሆነው ሁሉ ስቃይ ስላበቃ አስፈሪው ቅዥት አልፏል፡፡ አሁን ያን ስፍራ መጎብኘት ይቻላል፡፡
በዚህ ጊዜ በአውሽዊትዝ የሚሰቃይና የሚሞት የለም፡፡ ነገር ግን ገሃነም ለዘላለም ስቃይ እንደሆነ መፅሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ የኢየሱስ አካል እንደ ተሰቀለ ሆኖ የሚያሳይ ምስል በካምፑ መግቢያ ላይ ተመለከትኩ፡፡ ይህንም ምስል የሰራው በዚያ እስር ቤት ከነበሩት አንዱ እስረኛ በግድግዳው ላይ በመፋቅ ነበር፡፡ ይህ እስረኛ ምንም እንኳ በዚያ ስፍራ ቢሞትም ነገር ግን አዳኙን ኢየሱስን ያውቅ ነበር፡፡ በአሰቃቂ ስፍራ ቢሞትም በመንግሥተ ሰማያት ግን ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ከገለጸው ገሃነም ማንም ሰው ሊያመልጥ አይችልም (ለምሳሌ ማቴ 5፡29-30 ማቴ 7፡13 ማቴ 18፡8) አሰቃቂነቱ በሚቀጥልበት ስፍራ ገሃነምን መጎብኘት አትችልም፡፡

መንግሥተ ሰማያትም እንዲሁ ዘላለማዊ ናት ወደ እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር ሊወስደህ ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ግብዣ ራስህን ፈቃደኛ አድርግ፡፡ መንግሥቱን በመፈለግ የጌታን ስም ጥራ፡፡

አንዲት ሴት ከእኔ ጋር ከተወያየን በኋላ መፅሐፍ ቅዱስ ሰጠኋት እርሷ ግን እጅግ ተበሳጭታ ነበር፡፡ እንዴት አንድ መፅሐፍ መንግሥተ ሰማያት? ስትል አነጋገሯ የጉዞ ወኪል ይዘት ያለው ይመስል ነበር፡፡ ነገሩን በመስማማት የበረራ መፅሐፍ ከሌለሽ የምትደርሽበት ቦታ ለመድረስ አትችይም፡፡
ለምሳሌ ወደ ሃዋይ ደሴት ለመሄድ ትክክለኛውን ትኬት እንደምትፈልጊ ወደ ህይወት ለመሄድም ትክክለኛውን ትኬት ያስፈልግሻል ማለት ነው፡፡ ‹‹ነገር ግን ትኬቱን መግዛት ያስፈልጋል›› በማለት ስትመልስልኝ አዎ በእርግጠኝነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመሄድ ዋጋ መከፈል አለበት፡፡
ነገር ግን ይህንን ለመክፈል ማንም ሰው አይችልም እጅግ ውድ ነውና፡፡ እግዚአብሔር በመንግሥተ ሰማያት ኃጢአትን ማየትና ማለፍ ስለማይችል የእኛ ኃጢአት ወደዚያ እንዳንገባ ከልክሎናል፡፡ ስለሆነም አንቺ ለዘላለም ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ከፈለግሽ ከኃጢአት መዳን አለብሽ፡፡ ይህ ደግሞ የሚከናወነው ኃጢአት ባለወቀውና ሰው በሆነልን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ነው፡፡ እርሱ በደሙ በመስቀል ላይ ዋጋ በመክፈል ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንድንገባ ብቸኛ መንገድ ሆኗል፡፡

ስለዚህ ወደዚህ መንግሥት ለመግባት ምን ማድረግ አለብን? እግዚአብሔር ሁላችንንም በመፅሐፍ ቅዱስ ጥሪ እንድንታደም ይጋብዘናል፡፡

  •  በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም። (ሉቃ 13፡24)
  •  መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር። (ማቴ 4፡17)
  •  በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው። (ማቴ 7፡13-14)
  •  መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ።
    (1ጢሞ 6፡12)
  •  በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተሰዎችህም ትድናላችሁ አሉት። (ሐዋ 16፡31)

በዚህ መልዕክት ውስጥ ስሜትን የሚያነቃቃና የቶሎ በል ጥሪ አለ፡፡ ይህን ሁሉ ስትመለከት ከውስጥ የሆነ መልካምነት የተሞላበትና አስቸኳይ ጥሪ አንተን አብረህ ከዚህ በታች ካለው ፀሎት ጋር በመፀለይ ጥሪውን እንድትቀበል ለማድረግ ነው፡፡

ጌታ ኢየሱስ ሆይ ሕይወቴ ከአንተ መገኘት ውጪ ነበረች፡፡
ዛሬ አንተን ስለ ተረዳሁ ለመጀመሪያ ጊዜ በፀሎት ወደ አንተ እመጣለሁ፡፡ አሁን ግን መንግሥተ ሰማይና ገሃነም እንዳሉ ተረድቻለሁ፡፡ ገሃነም ከሚገባው ኃጢአቴና አለማመኔ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፡፡ ከአንተ ጋር በመንግሥትህ ለዘላለም መኖርን እፈልጋለሁ፡፡

አንተን በማመን እንጂ በራሴ በጎ ነገር መንግሥትህን መውርስ እንደማልችል ተረድቻለሁ፡፡ በእኔ ፈንታ በመስቀል ላይ በደሌን በመቀበል ተሸክመህ ዋጋዬንም ከፈልህ፡፡ አንተ ፍቅር ስለሆንህ ሞትክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ከልጅነት ጀምሮ ያለውን በደልና መተላለፍ እኔ የማውቀውን ብቻ ሳይሆን የማላስታውሰውን ኃጢአቶቼን፤ እኔ በፊትህ እንደሚነበብ መፅሐፍ ነኝ፡፡ በነዚህ ሁሉ ኃጢአት የኖርኩ ስለሆነ ወደ አንተ ህያው አምላክ መምጣት አልችልም መንግሥትህንም መውረስ አልችልም፡፡

ነገር ግን በኃጢአቴ ስለ ተፀፀትሁ ይቅር እንድትለኝ እማፀናለሁ፡፡ በፊትህ መልካም ያልሆነውን ሁሉ እንድተው እርዳኝ፡፡ መልካም የሆነውን ልማድ እንዲኖረኝና ቃልህን እንድረዳ እርዳኝ፡፡ የምትለኝን ለማስተዋል፤ ጥንካሬንም፤ ለማግኘትና ሃሴት በቃልህ እንዳገኝ እርዳኝ፡፡ የምሄድበትን ጎዳና አሳየኝ፡፡ የሚታዘዝህ ልብን ስጠኝ፡፡ ስለሰማኸኝ አመሰግናለሁ፡፡ አሁንም በአንተ ተስፋ በማመን ወደ አንተ መጥቻለሁ፡፡ አሁን የአንተ ልጅ ሆኛለሁ አንድ ቀን ደግሞ በመንግሥተ ሰማያት ከአንተ ጋር ለዘላለም እሆናለሁ፡፡ አሁን እንኳ አንተ በሁሉ ሁኔታ ከጎኔ ስለሆንህ ደስታዬም ተስፋዬም ሙሉ ነው፡፡

እባክህ አንተን ያመኑና የአንተን የእውነት ቃል የሚያስተምሩትን ሰዎችና ቤተ ክርስቲያንን እንዳገኝ እለምንሃለሁ አሜን››

Director and Professor Emeritus
Dr.-Ing. Werner Gitt